01

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፅ/ቤት

በ2025 ወሳኝ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎቿ ምቹ የሆነች ዘላቂ እና ችግሮችን መቋቋም የምትችል አዲስ አበባን ማየት፡፡ እንዲሁም፡-በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ተቋማት ምርታማነታቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ማሻሻል የሚያስችላቸው አቅም ተገንብቶ ማየትበከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥና ምርታማነትን የሚያሻሻል ተቋማዊ አቅም ተገንብቶ ማየት።የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አኗኗራቸው የተለወጠ ዜጎች።በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የመጠቀም ባህሉ የጎለበት ዜጋ ማፍራት፡፡በቴክኖሎጂ የበለጸገ ብቁና አምራች ዜጋ ማየት

02

ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት

በ2017 ዓ.ም አዲስ አበባ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብትና ደህንነት የተረጋገጠባት፤ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባት እና የስርዓተ-ፆታ እኩልነት የጎለበተባት ከተማ ሆና ማየት፡፡ ተልዕኮ /Mission/: በህብረተሰቡ ዘንድ የተዛባ የስርዓተ-ፆታ አመለካከትን በመቀየር፤ ማህበራዊ ችግሮች በመከላከል፤ መብትና ደህንነት በማስከበር፤ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት በማስፋፋት፣ የሴቶችን፣ሕፃናትና አካል ጉዳተኞችን ጉዳይ አካትቶ ትግበራ በማረጋገጥ ፣ ህብረተሰቡን በማሳተፍና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ በማቀናጀት እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን እና ሌሎች ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተስብ ክፍሎች ተሳትፎ አጎልብቶ በማብቃትና በማሸጋገር በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

03

ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ጽ/ቤት

በ2ዐ22ዓ.ም. የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሰረቶች አንዱ ማድረግ

04

ጤና ፅ/ቤት

ጤናማ፣ ምርታማና የበለጸገ ማህበረሰብ በ2022 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት ጥራቱን የጠበቀ፤ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት በመስጠት እና በመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ጤና ደህንነት መጠበቅ ነው፤

05

ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት

በ2022 ዓ.ም ከተማችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽ እና የተሟላ አሰራር ስርአት በመዘርጋት የተገልጋይ እርካታን እውን በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ማየት ነው፡

06

ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ በ2022 ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ እና ምርትና ምርታማነታቸው ያደገ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረው ማየት፤

07

አካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት

አዲስ አበባ ከተማ በ2017 ከአካባቢ ብክለት ተጠብቃ ውጤታማ የተፈጥሮ ኃብት አጠቃቀም የሚካሄድባት ለነዋሪዎቿ ጤናማና ተስማሚ የሆነች ተመራጭ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች አንዷ ማድረግ ነው፡፡