ስለ እኛ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ አስርአንድ (11) ክፍለ ከተሞች እንዱ የሆነው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 56. 71 እስኩየር ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በኢትዮጵያ ስታትስቲክ ኤጀንሲ ትንበያ መሠረት በ2014 ዓ.ም 363'100 (ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺ አንድ መቶ) ህዝብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት በ60/90 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የከተማ ግብርና ስራዎች፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና ማሻሻል፣ በመልካም አስተዳደር ፣የፀጥታ ስራውን በተቀናጀ መልኩ መስራት፣ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ ስራዎችን መከላከል፣ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ፣ በክረምትና በበጋ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን መስራት ችሏል የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የእሁድ ገቢያዎችን ከመፍጠርና ከማስፋፋት፣ የህብረት ስራ ማህበራት አቅርቦትና ስርጭትን የምርቶችን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ ማገናኘት የሚችል የእሁድ ገበያ 18 የነበረው ወደ 20 ማሳደግ በሸማች ህ/ስራ ማህበራት አምራቾችን ጨምሮ በተለያዩ ግብይቶች እና የገበያ ትስስር 9,539,494.72 ( ዘጠኝ ሚሊየን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ አራት መቶ ዘጠና አራት )ብር ማድረስ ተችሏል በህብረት ስራ ማህበራት በኩል የድጎማና የግብርና ምርቶች ስርጭትን አስመልክቶ በበጀት ዓመቱ 14,463 ኩንታል የግብርና ምርት፣ 54,756 ኩንታል ስኳር ፣ 901,723 ሊትር ዘይት፣ 4,629 የድጎማ ስንዴ ዱቄት ማሰራጨት ተችሏል በከተማ ግባርና በኩል የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ባለዉ አነስተኛ ቦታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የከተማ ግብርና ስራ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የነዋሪዉን የቤተሰብ የምግብ ፍጆታ እንዲሸፍን ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፅ/ቤት
በ2025 ወሳኝ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎቿ ምቹ የሆነች ዘላቂ እና ችግሮችን መቋቋም የምትችል አዲስ አበባን ማየት፡፡ እንዲሁም፡-በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ተቋማት ምርታማነታቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ማሻሻል የሚያስችላቸው አቅም ተገንብቶ ማየትበከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥና ምርታማነትን የሚያሻሻል ተቋማዊ አቅም ተገንብቶ ማየት።የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አኗኗራቸው የተለወጠ ዜጎች።በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የመጠቀም ባህሉ የጎለበት ዜጋ ማፍራት፡፡በቴክኖሎጂ የበለጸገ ብቁና አምራች ዜጋ ማየት
ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት
በ2017 ዓ.ም አዲስ አበባ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብትና ደህንነት የተረጋገጠባት፤ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባት እና የስርዓተ-ፆታ እኩልነት የጎለበተባት ከተማ ሆና ማየት፡፡ ተልዕኮ /Mission/: በህብረተሰቡ ዘንድ የተዛባ የስርዓተ-ፆታ አመለካከትን በመቀየር፤ ማህበራዊ ችግሮች በመከላከል፤ መብትና ደህንነት በማስከበር፤ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት በማስፋፋት፣ የሴቶችን፣ሕፃናትና አካል ጉዳተኞችን ጉዳይ አካትቶ ትግበራ በማረጋገጥ ፣ ህብረተሰቡን በማሳተፍና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ በማቀናጀት እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን እና ሌሎች ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተስብ ክፍሎች ተሳትፎ አጎልብቶ በማብቃትና በማሸጋገር በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ጽ/ቤት
በ2ዐ22ዓ.ም. የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሰረቶች አንዱ ማድረግ
ጤና ፅ/ቤት
ጤናማ፣ ምርታማና የበለጸገ ማህበረሰብ በ2022 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት ጥራቱን የጠበቀ፤ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት በመስጠት እና በመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ጤና ደህንነት መጠበቅ ነው፤
ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት
በ2022 ዓ.ም ከተማችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽ እና የተሟላ አሰራር ስርአት በመዘርጋት የተገልጋይ እርካታን እውን በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ማየት ነው፡
ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ በ2022 ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ እና ምርትና ምርታማነታቸው ያደገ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረው ማየት፤
Total Organization
Leaders
Workers
Documents
Services
Dolor Sitema
Minim veniam, quis nostrud exercitation ullamco laboris nisi ut aliquip ex ea commodo consequat tarad limino ata
Sed ut perspiciatis
Duis aute irure dolor in reprehenderit in voluptate velit esse cillum dolore eu fugiat nulla pariatur
Magni Dolores
Excepteur sint occaecat cupidatat non proident, sunt in culpa qui officia deserunt mollit anim id est laborum
Nemo Enim
At vero eos et accusamus et iusto odio dignissimos ducimus qui blanditiis praesentium voluptatum deleniti atque
Eiusmod Tempor
Et harum quidem rerum facilis est et expedita distinctio. Nam libero tempore, cum soluta nobis est eligendi
Contact Us
Our Address
Addis Ababa, Megenagna
Email Us
info@smartyeka.gov.et
contact@smartyeka.gov.et
Call Us
+251 --- -- --
+251 --- -- --